Jump to content

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት

ከውክፔዲያ
የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት

የጦርነቱ ታሪክ በካርታ
ቀን ከሐምሌ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ እስከ ኅዳር ፪ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም.
ቬርሳይ ውል የተፈረመው ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም.
ቦታ አውሮፓ፣ አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ የፓሲፊክ ደሴቶች፣ ቻይና እና ከደቡብ አሜሪካ ጠረፍ አካባቢ
ውጤት የአላይድ /allied/ ሀገሮች ድል
  • የአለማኛ፣ ሩሲያ፣ ኦቶማን እና አውስትሪያ ሀንጋሪ መንግሥታት መውደቅ
  • አዲስ ሀገራት በአውሮፓና መካከለኛው ምሥራቅ ተመሠረቱ
  • የአለማኛ ቅኝ ግዛቶችና የኦቶማን ክልሎች ወደ ሌሎች ሀገራት ተላለፉ
  • የዓለም መንግሥታት ማኅበር ተቋቋመ
ወገኖች
አላይድ ሀገራት

ፈረንሣይ ፈረንሣይ
 ብሪታንያ
 የሩሲያ መንግሥት (1914–17 እ.ኤ.አ.)
 አሜሪካ (1917–18 እ.ኤ.አ.)
 ጣሊያን (1915–18 እ.ኤ.አ.)
 ጃፓን
 ቤልጅግ
 ሰርቢያ
 ሮማንያ (1916–18 እ.ኤ.አ.)
 ግሪክ (1917–18 እ.ኤ.አ.)
ፖርቱጋል ፖርቱጋል (1916–18 እ.ኤ.አ.)
 ሞንቴኔግሮ (1914–16 እ.ኤ.አ.)
 ብራዚል (1917–18 እ.ኤ.አ.)
እና ሌሎችም

መካከለኛው ኃያላት /central powers/

 የጀርመን መንግሥት
 አውስትሪያ ሀንጋሪ
 የኦቶማን መንግሥት
 ቡልጋሪያ (1915–18 እ.ኤ.አ.)

መሪዎች
ፈረንሣይ ሬይመንድ ፑዋንካሬ

ፈረንሣይ ጊዮርጊስ ክሌሜንኮ
ፈረንሣይ ፈርዲናንድ ፎሽ
የብሪታንያ መንግሥት ኧርበርት ሄንሪ አስክዊዝ
የብሪታንያ መንግሥት ዴቪድ ሎይድ ጆርጅ
የሩሲያ መንግሥት ኒኮላይ ፪ኛ
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) አንቶንዮ ሳላንድራ
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) ቪቶሪዮ ኢማኑኤል ኦርላንዶ
አሜሪካ ዉድሮው ዊልሰን
እና ሌሎችም

የጀርመን መንግሥት ዊልሄልም ፪ኛ

የጀርመን መንግሥት ፖል ቮን ሂንደንበርግ
የጀርመን መንግሥት ኤሪክ ሉደንዶርፍ
አውስትሪያ ሀንጋሪ ፍራንዝ ጆሴፍ
አውስትሪያ ሀንጋሪ ካርል ፩ኛ
የኦቶማን መንግሥት ኢስማኤል ኤንቨር
የቡልጋሪያ መንግሥት ፈርዲናንድ ፩ኛ
እና ሌሎችም

አቅም
የሩሲያ መንግሥት 12,000,000

የብሪታንያ መንግሥት 8,841,541[1]
ፈረንሣይ 8,660,000[2]
የጣሊያን መንግሥት (1861–1946 እ.ኤ.አ.) 5,093,140
አሜሪካ 4,743,826
የሮማንያ መንግሥት 1,234,000
የጃፓን መንግሥት 800,000
የሰርቢያ መንግሥት 707,343
ቤልጅግ 380,000
የግሪክ መንግሥት 250,000
ፖርቱጋል 200,000
የሞንቴኔግሮ መንግሥት 50,000
ጠቅላላ፦ 42,959,850

የጀርመን መንግሥት 13,250,000

አውስትሪያ ሀንጋሪ 7,800,000
የኦቶማን መንግሥት 2,998,321
የቡልጋሪያ መንግሥት 1,200,000
ጠቅላላ፦ 25,248,321

የደረሰው ጉዳት
የሞቱ፦
5,525,000
የቆሰሉ፦
12,831,500
የጠፉ፦
4,121,000
ጠቅላላ፦
22,477,500
የሞቱ፦
4,386,000
የቆሰሉ፦
8,388,000
የጠፉ፦
3,629,000
ጠቅላላ፦
16,403,000

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነትአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

ለጦርነቱ ቅስቀሳ ብዙ ምክንያቶች በታሪክ ምሑራን ይጠቀሳሉ። ዓቢይ ከሚባሉት ነገሮች ግን የወቅቱ ኃያላን መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ተልዕኮዎች ሲሆኑ የክብሪቱ መጫሪያ ምክንያት ግን የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽአውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው። የሳቸውን መገደል ምክንያት በማድረግ የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትሰርቢያ ንጉዛት ሊያሟሉት የማይችሉትን፣ አስር ነጥብ ያዘለ የእላፊ ገደብ (ultimatum) ማስጠንቀቂያ ይሰጡና ገደቡ ሲያልፍ ቅድሚያውን እንደወጠኑት በሰርቢያ ላይ የጦር አዋጅ አወጁ። ይሄም የታቀደ ትንኮሳ ከአስር ዓመታት በፊት ተመሥርተው የነበሩትን ብዙ የትብብር ውሎችን የሚያንቀሳቅስ ሁኔታ ስለነበረ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁሉንም ኃያላን መንግሥታት ጦርነቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስገደዳቸው። እያንዳንዳቸው ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚያስተዳድሯቸው ቅኝ ግዛቶች ስለነበሯቸው እነዚህንም ቅኝ ግዛቶች በዚሁ ግብግብ ተሳታፊ አደረጋቸው።

የጦርነቱ መግቢያ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጦርነቱ ትርዒት የተከፈተው የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ሠራዊት ሰርቢያን ሲወሩ አጋራቸው የአለማኛ መንግሥት ደግሞ ቤልጂግን፣ ሉክሳምቡርግን እና ፈረንሳይን ወረረ። በተቃራኒው ደግሞ የሩሲያ ሠራዊት የምዕራብ አለማኛን ግዛት ይወራሉ። የኦቶማን ንጉሠ ነገሥት ሠራዊት ደግሞ ወዲያው ጦርነቱ ውስጥ ሲገባ በቀጣዩ ዓመት ኢጣልያቡልጋሪያ ተከትለው ገቡበት። የሩሲያ ሠራዊት ለሦስት ዓመታት ከተዋጋ በኋላ የጥቅምት አብዮት፲፱፻፲ ዓ/ም ሲፈነዳ ከዚህ ታላቅ ጦርነት ወጣ።

አለማኛ ሠራዊት በ፲፱፻፻፲ ዓ/ም የምዕራብ የጦርነቱን ግንባር ማጥቃት ከጀመሩ በኋላ የአሜሪካ ሠራዊት ከአጋሮቹ ጋር ሲሰለፍ፣ የምዕራብ አገሮች ቡድን አለማኞቹን በማጥቃት እያቸነፏቸው መጡ። መጨረሻ ላይ ተሸናፊው የአለማኛ ሠራዊት መሸነፉን አምኖ ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የእጅ መስጫ ውል ሲፈርም፤ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም የተለኮሰው ጦርነት አከተመ። አብሮትም የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ግዛት፣ የኦቶማን ግዛት ሲጠፉ የጀርመን እና የሩሲያ ኃያልነት በፖለቲካም ሆነ በጉልበት ተደምስሰው የአራቱንም ቅኝ ግዛቶች አሸናፊዎቹ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ተከፋፈሏቸው።

የአንደኛው ዓለም ጦርነት ተስቦ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀድሞ ኃያላን መንግሥታትትን ውድመት ያስከተለ ክስተት ከመሆኑም ሌላ፤ በመካከለኛ አውሮፓ የብዙ ትናንሽ ሉዓላዊ አገሮችን መወለድ፤ የዓለም መንግሥታት ማኅበርን መቋቋሚያ መንስዔ፤ ከሁሉም በላይ ግን በአውሮፓ አኅጉር የብሔራዊነትን መንፈስ የቀሰቀሰና የጀርመን ሽንፈትን ያረጋገጠው የቬርሳይ ውል (Treaty of Versailles) በጀርመኖች ላይ ያስከተለው የጭቆና ስሜት አገራችን ኢትዮጵያ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ ስትወረር የተለኮሰውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት መሆኑ ነው።

  1. ^ Figures are for the British Empire
  2. ^ Figures are for Metropolitan France and its colonies

የውጭ መያያዣ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።
  翻译: