Jump to content

ጄረሚ ቤንታም

ከውክፔዲያ
ጄረሚ ቤንታም

ጄረሚ ቤንታም (እ.ኤ.አ ከካቲት 15 ቀን 1748 እስከ  ሐምሌ 6 ቀን 1832 ዓ.ም) የነበረ እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ የሕግ ተማሪ እና ማህበረሰብ አዳሽ ነበር። በአሁኑ ዘመን ጠቃሚያዊነት (ዩትልተሪያኒዝም) እና የእንስሳት መብት መከራከርን የጀመረ መሆኑ ይታወቃል።

ቤንታም የለዘብተኝነት (ሊብራሊዝም) ዋና ተሟጋች እንደሆነም ይነገራል። ቤተ እምነትና መንግስት እንዲለያዩም ይደግፍ ነበር። የሴቶች እኩልነት፣ የመፋታት መብት፣ የባርነት መቅረትን፣ የሞት ፍርድ መቅረትን፣ አካላዊ የሰዎች ቅጣት መቅረትን፣ የአንድ አይነት ጾታ ግንኙነት ወንጀል መሆን መቆምን፣ ፓንቶኮፖን የሚባለውን የእስር ቤት አይነት ስራን፣ የመናገር ነጻነትን የወልድ ብድርንና ባጠቃላይ መልኩ ዘመናዊ ለዘብተኞች የሚድግፏቸውን አቋሞች ይደግፍ ነበር። ተማሪዎቹ፣ ጆን ስቱዋርት ሚል እና ሶሺያሊዝምን የፈለሰፈው ሮበርት ኦወን የለዘብተኝነት ርዕዮተ-ዓለምን በማስፋፋት ስሙን እንዲገን አስተዋጽዖ አድርገዋል። ቤንታም ለግለሰብና ለኢኮኖሚክ ነጻነት ተሟጋች ነበር።

በአጠቃላይ መልኩ ቤንታም በዘመናዊ አስተያየቶች ላይ በራሱ ስራና በተማሪዎቹ (ለምሳሌ ስቱዋርት ሚል እና ሶሺያሊዝምን ፈጣሪው ሮበርት ኦወን) ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደረገ ሰው ነበር። ስለሆነም በብዙዎች ዘንድ እንደሚታመነው በታሪክ ዋናው የጠቃሚያዊነት ፍልስፍና አራማጅ ይሄው ሰው ነበር።

  翻译: