ዲ ኤን ኤ ( Deoxyribonucleic Acid) በጣም ትልቅ ሞልዩኪል ሆኖ ህይወት ያላቸውን ማናቸውንም ፍጡራን፣አትክልትእንስሳትባክቴሪያ ወዘተ የዘር-ቀመር (ጄኔቲክ ኮድ) ያዘለ ነው። የአንድ ፍጡር ዲ ኤን ኤ በዚያ ፍጡር ማናቸውም ህዋስ (ሴል) ውስጥ ይገኛል። የመገኘቱ ውጤት እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ፍጡር የራሱ የሆነ ልዩ ባህርይ እንዲኖረው ያደርጋል። ይህንም እሚያደርገው የፍጡሩ አካላት መገንቢያ የሆኑ የፕሮቲን ሞለኪሎችን በትዕዛዝ በተወሰነ መልኩ እንዲሰሩ ዲ ኤን ኤ ስለሚመራ ነው። የአንድ ህዋስ ፕሮቲን የዚያን ህዋስ ተግባር ይወስናል። ዲ ኤን ኤ ከወላጅ ወደ ልጅ ይተላለፋል፣ ስለሆነም ወላጆችና ልጆች ተቀራራቢ ባህርይ እንዲኖራቸው ያደርጋል። አንድ አይነት የማይሆኑበት ምክንያት ልጆች ከሁለቱ ወላጆች ድብልቅ ዲኤን ኤ ስለሚዎርሱ ነው።

ህይወት ካላቸው ነገሮች ሁሉ ቫይረሶች ለየት ይላሉ። በመጀመሪያ ደረጃ ቫይረሶች ህይወት ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል። በተጨማሪይ ቫይረሶች በሁለት ይከፈላሉ፣ ገሚሶቹ እንደሌሎች ፍጡራን ዲ ኤን ኤ ሲኖራቸው ገሚሶቹ ደግሞ አር ኤን ኤ ብቻ ይኖራቸዋል። ዲኤንኤ ያላቸው ቫይረሶች ሌሎች ህዋሳትን የሚያጠቁት አስኳሉ ውስጥ በመግባት ሲሆን አር ኤን ኤ ብቻ ያላቸው ደግሞ የህዋሱ ሳይቶፕላዝም ውስጥ ነው። ኤድስን የሚፈጥረው የ ኤች አይ ቪ ቫይረስ ከኋለኞቹ ወገን ነው።

ዲ ኤን ኤ ከሥነ ቅመማ አንጻር ከኑክሊክ አሲድ ( nucleic acid) የተሠራ ሲሆን በመቶ ሚልዮን በሚቆጠሩ የተጣመዱ ኒኩልቲዲም ሁለትም ጥምዝ መሰላ ይሰራሉ፡፡ ይህ ጥምዝ መሰላል የሁሉን ዝርያ መረጃ የያዘ ሲሆን በሴል ላሉ ፕሮቲኖችህ መገንቢያ መልጅ የያዘ ነው።

  翻译: