Enderase Youth Assocation reposted this
ይህንን በቶሎ ተረዳ ህይወት በውጭ ያለው አይደለም ህይወት የውስጥ ነው ምንጩም ከልብ ከውስጠኛው የሰወነት ክፍል ነው።ተፈጥሮ ይህንን በግልጽ ያስረዳናል በቀላሉ እንኳን ብንመለከት የሰው መፀነስ ፣መረገዝ ፣ የመጀመሪያ እድገት የውስጥ ሂደት እና ውጤት ነው።የድርጊቶቻችን መንስኤ እንኳን የማናየው ሀሳብ የውስጥ ሰውነታችን ውጤት ነው። ሰው የተፈጠረው አካባቢወን ፣መኖሪያውን እና ዓለሙን በህይወቱ ተዕጽኖ በመፍጠር እንዲመራ እንጂ ደመናው ሲጠቁር ፊቱ በሀዘን እንዲመታ አየሩ ነፋሻማ እና የፈካ ሲሆን ፊቱ እንዲያበራ አይደለም። ዓለምን በፈጠራ ስራቸው በምርምር ስራቸው በጥበብ አስደናቂ መልዕክቶቻቸው የቀየሩ ጥቂት ሰዎች የዚህ የህይወት መገለጥ የተረዱ ሰዎች ናቸው ለዛነው ቶማስ ኤዲሰን ያለበት ዓለም ምንም የጨለመ ቢሆንም በልቡ የበራው እና በዓለም ሁሉ ሲበራ ያየውን ብርሃን በብዙ ትችት እንዲሁም የብዙ ጊዜ የእርሱ መሳሳት እና መውደቅ አላስቆመውም። በውስጥህ ምንድነው የሞላው ብዙ ቀልዶች ወይስ ቁምነገሮች ፣ ሌላውን ረግጦ የመበልፀግ ህልም ወይስ ለሌላው በረከት የመሆን መሻት ፣ ዝነኛ ሆኖ የራስን ስም የመስቀል ትግል ወይስ ሌላውን ከፊት የማስቀደም ትልም ሰው በልቡ የሞላው ብቻ ነው በአፉ የሚፈሰው በህይወትም እንደዚያው እንግዲያውስ ዛሬ ዕወቅበት በጆሮ እና በዓይን ምታስገባው የውስጥ መብልን ለይበት ምክንያቱም LIFE IS FROM INSIDE OUT. መልካም ሳምንት !