Jump to content

ሏንዳ

ከውክፔዲያ

ሏንዳ (Luanda) የአንጎላ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1996 ዓ.ም.) 4.5 ሚሊዮን ሆኖ ይገመታል። ከተማው 08°50′ ደቡብ ኬክሮስ እና 13°15′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ከተማው በ1567 ዓ.ም. ሳን ፓውሎ (ቅዱስ ጳውሎስ) ዴ ሏንዳ ተብሎ በፖርቱጋላዊው ፓውሎ ዲያስ ዴ ኖቫይስ ተመሠረተ። ከ1619 ዓ.ም. ጀምሮ የአንጎላ መቀመጫ ሆኗል። ነገር ግን ከ1632 እስከ 1640 ዓ.ም. ድረስ የሆላንድ ሰዎች ይዘውት ስሙን ፎርት አርደንግቡርግ አሉት።

አብዛኛው የአንጎላ የትምህርት ተቋማት በዚህ ከተማ ነው የሚገኙት። የአንጎላ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ እና አጎስቲኖ ኒቶ ዩኒቨርሲቲ ምሳሌ ናቸው። ኤስታዲዮ ዳ ሲዳዴላ (Estádio da Cidadela) የሚባለው የአንጎላ ዋና ስታዲየምም በሏንዳ ይገኛል።

የሏንዳ የህዝብ ዕድገት ከ1750 እ.ኤ.አ. ጀምሮ

እህት ከተማዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


  翻译: